ስለ አዘጋጁ
ዶ/ር ፍቃዱ አየለ ለጤና አገልግሎት እና ለጤና መረጃዎች ተደራሽነት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ የነበሩ ከ20 ዓመት በላይ ልምድ ያላቸው የተመሰከረላቸው ኢትዮጵያዊ ቀዶ ጠጋኝ ሐኪም ናቸው። የሕክምና ዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከጎንደር ዩንቨርሲቲ የአጠቃላይ ቀዶ ሕክምና ልዩ ሐኪምነትን በ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አጠናቀዋል።
ዶ/ር ፍቃዱ እንደ አጠቃላይ ቀዶ ሕክምና ባለሙያ ህይወት አዳኝ ቀዶ ጥገናዎችን በማድረግ እና በሜዲካል ዳሬክተርነት ደግሞ ልዩ ልዩ የጤና ድርጅቶችን በመምራተ ሰርተዋል።
በአሁኑ ሰአት ተቀማጭነታቸው በአሜሪካ ሲሆን በጤና ላይ ያላቸውን አስተዋጽኦ ጤና ነክ የሆኑ ጽሁፎችንና ትምህርቶችን በማቅረብ ቀጥለዋል።
ከእኛ ገር ይወያዩ
ጤናና ጤናነክ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጥያቄዎችን፣ አስተያየቶችን እና በዚህ ድህረ ገጽ ቢቀርብ የሚሉትን ጉዳይ ያሳውቁን።